EthioPassNew                                                                                   

 የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ማወቅ የሚገባዎ አንዳንድ ነጥቦች፣

 • እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንሰጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ፎቶኮፒያቸው አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ።
  በኢትዮጵያ ኢሚግሬሽንና የዜግነት ጉዳይ ዋና መምሪያ ሲሰጥ የነበረው አዲሱ ማሽን ሪደብል  ፓስፖርት  እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 2010  ጀምሮ 
  በኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽ/ቤቶች አማካኝነት ወደ አገር ቤት በመላክ ተሰርቶ የመጡትን የአገልግሎት ጥያቄዎች ለባለጉዳዮች የሚደርስበት
  አሠራር ስለተዘረጋ  እባክዎ  ከጉዞ  ወይም ከታደሰ ፓስፖርት ጋር በተያያዘ  አገልግሎት  ከመጠየቅዎ  ቢያንስ 45 ቀናት  አስቀድመው
  ማመልከት ይጠበቅብዎታል። 
 • አዲሱን ማሽን ሪደብል ፓስፖርት ለማግኘት የጣት አሻራ ማቅረብ ያስፈልጋል። ነገር ግን ከዚህ  ቀደም አዲሱን ፓስፖርት ሲወስዱ
  የጣት አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ መስጠት አያስፈልግዎትም። እድሜአቸው ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት አሻራ መስጠት
  አይጠበቅባቸውም፤ ሆኖም ከዚህ ቀደም ከ14 ዓመት በታች በመሆናቸው ምክንያት ያለ አሻራ አዲሱ ፓስፖርት ተዘጋጅቶላቸው
  ከነበረና አሁን ከ14 ዓመት እና በላይ ከሆኑ የጣት አሻራ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
 • ወላጆች/አሳዳጊዎች ከ18 ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች አዱሱ ማሽን ሪደብል ፓስፖርት እንዲታደስላቸው ጥያቄ ሲያቀርቡ የልጆችን 
  የልደት ሰርተፊኬት ከማመልከቻው ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል። 
         
 • ፓስፖርት ተዘጋጅቶ እስከሚደርስዎ ድረስ መቆየት የማይችሉና በተለያየ አጣዳፊ ምክንያቶች በአስቸኳይ ወደ አገር ቤት መሄድ ከፈለጉ
  ወደ አገር ቤት መግቢያ የሚያገለግለውን ሊሴፓሴ ብቻ (የሊሴ ፓሴ አገልግሎት የሚለውን ይክፈቱ)ወስደው ከአገር ቤት ፓስፖርት
  ማመልከት ይገባዎታል።
 • የፓስፖርትና የሊሴፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከኤምባሲው ወደ አገር ቤት ከተላከ
  ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ኤምባሲው ማመልከቻዎን አገር ቤት ከላከ አንድ
  ወርና ከዚያ በላይ  ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ ጉዞዎ ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ ከኢሚግሬሽንና የዜግነት
  ጉዳይ ዋና መምሪያ ፓስፖርትዎን መረከብ ይችላሉ።
 • ኤምባሲው ፓስፖርትዎን ለማዘጋጀት ተጨማሪ ማስረጃዎች እንዲያቀርቡ ሲጠይቅ፣ እባክዎ በተነገረዎት በሳምንት ጊዜ ውስጥ
  ማስረጃውን ይላኩልን። ሆኖም ማስረጃውን እንዲልኩ ለ3ኛ ጊዜ ተገልጾልዎት ከሆነና በወቅቱ ካላቀረቡ ፋይልዎ ተመላሽ ተደርጎ
  እንደ አዲስ ማመልከት ይጠበቅብዎታል።

የአገልግሎት ጥያቄ  ዓይነቶች፣
1. አገልግሎቱ ያለቀ/ ያበቃ ፓስፖርት መቀየር/ ማደስ፣
2. በጠፋ ፓስፖርት ምትክ አዲስ ፓስፖርት ማግኘት፣

3. በወላጆቻቸው ፓስፖርት ላይ ተመዝግበው ሲጓዙ ለነበሩ ህጻናት አዲስ ፓስፖርት ማውጣት፣ 

1. አገልግሎቱ ያለቀ/ ያበቃ ፓስፖርት መቀየር/ ማደስ፣
አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መሥፈርቶች:-
ሀ. አራት(4) 3 ሲ/ሜ በ 4 ሲ/ሜ መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ከለር ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣
    መደቡ ነጣ ያለና  ከጀርባው
  የአመልካች ሙሉ ሥም የተጻፈበት)፣
ለ. ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ዋናው ፓስፖርት ማቅረብ፣
ሐ. ለመቀየር ወይም ለማደስ የተፈለገው ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ሥም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ
     ጊዜ የታደሰበት
ገጽ የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ማቅረብ፣
መ. በካናዳ አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ዋናውን ማስረጃ ከሁለት ኮፒ ጋር ማቅረብ፣

       *** ቋሚ የካናዳ የመኖሪያ ፈቃድ (PRC)፣ ወይም

       *** ቋሚ የካናዳ የመኖሪያ ፈቃድ (PRC)ከሌለዎ የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያስረዳ ማስረጃ፣ ወይም

       *** የሥራ ፈቃድ (Work permit) ፣ ወይም

       *** የትምህርት ፈቃድ (Study permit)

ሠ. የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጻፈ መኒ ኦርደር /money order/ ሆኖ

ተራ ቁ.      ፓስፖርት             የአገልግሎት ክፍያ በካናዳ ዶላር                 ምርመራ               
 1  ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት               77 CAD  
 2   ባለ 48 ገጽ ፓስፖርት               103 CAD   በኤምባሲው አገልግሎቱ መሰጠት አልተጀመረም።
 3   ባለ 64 ገጽ ፓስፖርት              141CAD  በኤምባሲው አገልግሎቱ መሰጠት አልተጀመረም።

ረ. የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ
    ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብልዎ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/ Form/ ላይ አሻራዎን
    ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ/ማቅረብ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው
    በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።
    (Click here to download Finger print Capture FORM) 
ሰ. የማመልከቻ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት (Click here to download FORM)
ሸ. አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፖስታ Tracking Number ያለው ቅድሚያ የተከፈለበት አስቸኳይ ወይም
    የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም FedEX ወይም UPS.
top

 2. በጠፋ ፓስፖርት ምትክ አዲስ ፓስፖርት ማግኘት፣
አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መሥፈርቶች:-
ሀ. አራት(4) 3 ሲ/ሜ በ 4 ሲ/ሜ መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ከለር ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣
    መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው
  የአመልካች ሙሉ ሥም የተጻፈበት)፣
ለ. የቀድሞ ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ሥም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበት ገጽ 
    
የሚያሳይ በሁለት ኮፒ ማቅረብ፣
ሐ. የፓስፖርትዎን ኮፒ ማግኘት ካልቻሉ፣ የጠፋው ፓስፖርት ቁጥር፣ የትና መቼ እንደወሰዱት እንዲሁም የቤተሰብዎን የአገር ቤት
    ሙሉ አድራሻና ስልክ ቁጥር በመጥቀስ ማመልከቻ ጽፈው ማቅረብ እና በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ
    የልደት የምስክር ወረቀት ከሁለት ኮፒ ጋር ማቅረብ፣
መ. በካናዳ አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ዋናውን ማስረጃ ከሁለት ኮፒ ጋር ማቅረብ፣

       *** ቋሚ የካናዳ የመኖሪያ ፈቃድ (PRC)፣ ወይም

       *** ቋሚ የካናዳ የመኖሪያ ፈቃድ (PRC)ከሌለዎ የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያስረዳ ማስረጃ፣ ወይም

       *** የሥራ ፈቃድ (Work permit) ፣ ወይም

       *** የትምህርት ፈቃድ (Study permit) እና

       *** ዝርዝር የፖሊስ ሪፖርት፣

ሠ. የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጻፈ መኒ ኦርደር /money order/ ሆኖ

ተራ ቁ.     የአገልግሎት ዓይነት             የአገልግሎት  ክፍያ      
 1  ለመጀመሪያ ጊዜ ለጠፋ ፓስፖርት ምትክ ሲጠየቅ በመደበኛ ክፍያ ላይ 50% ተጨማሪ
 2   ለሁለተኛ ጊዜ ለጠፋ ፓስፖርት ምትክ ሲጠየቅ በመደበኛ ክፍያ ላይ  100 % ተጨማሪ
 3   ለሦስተኛ ጊዜ ለጠፋ ፓስፖርት ምትክ ሲጠየቅ በመደበኛ ክፍያ ላይ 200 % ተጨማሪ

ረ. የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ
    ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብልዎ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/ Form/ ላይ አሻራዎን
    ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ/ማቅረብ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው
    በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።
    (Click here to download Finger print Capture FORM) 
ሰ. የማመልከቻ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት (Click here to download FORM)
ሸ. አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፖስታ Tracking Number ያለው ቅድሚያ የተከፈለበት አስቸኳይ ወይም
    የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም FedEX ወይም UPS.
top

 3. በወላጆቻቸው ፓስፖርት ላይ ተመዝግበው ሲጓዙ ለነበሩ ህጻናት አዲስ ፓስፖርት ማውጣት፣ 
አገልግሎቱን ለማግኘት መሟላት የሚገባቸው መሥፈርቶች:-
ሀ. አራት(4) 3 ሲ/ሜ በ 4 ሲ/ሜ መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6 ወር ወዲህ የተነሱት ከለር ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች
    የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና  ከጀርባው
  የአመልካች ሙሉ ሥም የተጻፈበት)፣
ለ. ከወላጆቻቸው ጋር የተጓዙበትን ፓስፖርት እና የተረጋገጠ የልደት የምስክር ወረቀት በሁለት ኮፒ፣
ሐ. በካናዳ አገር ያሉበትን ስታተስ የሚያሳይ ዋናውን ማስረጃ ከሁለት ኮፒ ጋር ማቅረብ፣

       *** ቋሚ የካናዳ የመኖሪያ ፈቃድ (PRC)፣ ወይም

       *** ቋሚ የካናዳ የመኖሪያ ፈቃድ (PRC)ከሌለዎ የኢሚግሬሽን ስታተስዎን የሚያስረዳ ማስረጃ፣ ወይም

       *** የሥራ ፈቃድ (Work permit) ፣ ወይም

       *** የትምህርት ፈቃድ (Study permit)
መ. የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጻፈ መኒ ኦርደር /money order/ ሆኖ

ተራ ቁ.      ፓስፖርት             የአገልግሎት ክፍያ በካናዳ ዶላር                 ምርመራ               
 1  ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት             77 CAD  
 2   ባለ 48 ገጽ ፓስፖርት           103 CAD   በኤምባሲው አገልግሎቱ መሰጠት አልተጀመረም።
 3   ባለ 64 ገጽ ፓስፖርት            141 CAD  በኤምባሲው አገልግሎቱ መሰጠት አልተጀመረም።

ረ. የጣት አሻራ ማቅረብ ለሚጠበቅባችሁ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ
    ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብልዎ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/ Form/ ላይ አሻራዎን
    ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ/ማቅረብ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው
    በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።
    (Click here to download Finger print Capture FORM) 
ሰ. የማመልከቻ ቅጽ በሁለት ኮፒ መሙላት (Click here to download FORM)
ሸ. አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፖስታ Tracking Number ያለው ቅድሚያ የተከፈለበት አስቸኳይ ወይም
    የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም FedEX ወይም UPS.
top

Embassy's Address

 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org

Copy right ©2014 - Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, Ottawa, Canadan