ሀ. የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ ለመጀመሪያ ጊዜ መታወቂያ ካርዱን ሲጠይቅ
ለ. አካለ መጠን ላልደረሰ የኢትዮጵያ ተወላጅ ልጅ ስለሚሰጥ አገልግሎት፤
ሐ. የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖሯቸው ለትዳር ጓደኛቸው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ሲጠይቁ
መ. የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የአገልግሎት ዘመኑ በማለቁ ለማሳደስ ሲጠይቁ
ሠ. በጠፋ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ
ረ. በተበላሸ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ምትክ ሲጠይቁ
ሀ. የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ ለመጀመሪያ ጊዜ መታወቂያ ካርድ ሲጠይቅ፣
1. መጠየቂያ ቅጽ-1 በሁለት ኮፒ መሙላት (Click here to download)
2.የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት(አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6ወራት የፀና ፓስፖርት)ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ
የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ ፣
3.በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆንን የሚያስረዳ ማስረጃ፣
4.የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ
በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና
ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት
አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።
(ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture FORM)
5.ሦስት(3)የፓስፖርት መጠን (3x4cm)ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች
የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም የተጻፈበት)፣
6.የአገልግሎት ክፍያ 264.00 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር/money order/
7.አድራሻዎ የተጻፈበት ቅድሚያ የተከፈለ አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number
ያለው (FEDEX ወይም UPS) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
TOP
ለ.አካለ መጠን ላልደረሰ የኢትዮጵያ ተወላጅ ስለሚሰጥ አገልግሎት፣
1. ዕድሜው 18 ዓመት ያልሞላው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የተቀበለ የውጭ ዜግነት ያለው ሰው ልጅ
በወላጅ አማካኝነት የሚከተሉት ሲሟሉ:-
1.1 መጠየቂያ ቅጽ-1 በሁለት ኮፒ መሙላት (Click here to download)
1.2 የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት (አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6ወራት የፀና ፓስፖርት) ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ
የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ ፣
1.3 የልጁ የተረጋገጠና ሕጋዊ የልደት የምስክር ወረቀት (በኖታሪ ፐብሊክ እና በሚመለከተው የውጭ ጉዳይ መ/ቤት በኩል የተረጋገጠ)
ዋናው ከሁለት ቅጅ ጋር፣
1.4 የወላጅ የአገልግሎቱ ጊዜው ያላበቃ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ
የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ ፣
1.5 ሦስት(3) የፓስፖርት መጠን (3x4cm) ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች
የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም የተጻፈበት)፣
1.6 ዕድሜያቸው 14 ዓመት የሆናቸው፣ ከ14 ዓመት በላይና 18 ዓመት ያልሞላቸው ልጆች አሻራ መስጠት ይኖርባቸዋል።
የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ በመሄድ
ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/ form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን መላክ።
ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ
መጠቀም ይችላሉ። (ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture FORM)
1.7 የአገልግሎት ክፍያ 26.40 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር/money order/
1.8 አድራሻዎ የተጻፈበት ቅድሚያ የተከፈለ አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number
ያለው (FEDEX ወይም UPS) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
Top
ሐ. የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖሯቸው ለትዳር ጓደኛቸው የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ
ካርድ ለሚጠይቁ፣
1.መጠየቂያ ቅጽ-2 በሁለት ኮፒ መሙላት (click here to download)፣
2.የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት ግለሰብ አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6ወር የፀና የውጭ አገር
ፓስፖርት ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
3.ከተሰጠበት ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት የተረጋገጠ የጋብቻ ምስክር ወረቀት ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ
ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣ (ጋብቻው ቢያንስ ለሁለት ዓመት የፀና መሆን ይኖርበታል።)
4.መታወቂያው እንዲሰጥ የሚወሰነው ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ መሃላ ሰነድ ተያይዞ ሲቀርብ
ነው። (Click here to download BOTH FORMS) /ቅፅ-7/ እና /ቅፅ-8/
5.የባል ወይም የሚስት አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እና የትውልድ መታወቂያውን
ለማግኘት በማስረጃነት አቅርበውት የነበረው ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱን
ማስረጃ ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
6.የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት/ላት ግለሰብ ሦስት/3/ የፓስፖርት መጠን(3x4cm)ያለውና
ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም
የተጻፈበት)፣
7.የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የሚጠየቅለት/ላት ግለሰብ የጣት አሻራ ማቅረብ ይጠበቅበታል/ባታል።
የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች
ዘንድ በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው
ዋናውንና ኮፒውን መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል
የተዘጋጀውን የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።
(ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture FORM)፣
8.የአገልግሎት ክፍያ 264.00 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ መኒ ኦርደር/money order/፣
9.አድራሻዎ የተጻፈበት ቅድሚያ የተከፈለ አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number
ያለው (FEDEX ወይም UPS) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
TOP
መ.የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ የአገልግሎት ዘመኑ በማለቁ ለማሳደስ ሲጠየቅ፣
1.መጠየቂያ ቅጽ-3 በሁለት ኮፒ መሙላት (Click here to download)፣
2.የአገልግሎት ዘመኑ ያበቃው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ዋናውንና ሁለት ኮፒ፣
3.በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆንን የሚያስረዳ ማስረጃ፣
4.አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6ወር የፀና የውጭ አገር ፓስፖርት ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት
ኮፒ፣
5.ሦስት/3/ የፓስፖርት መጠን(3x4cm) ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች
የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም የተጻፈበት)፣
6.በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እድሳት ጥያቄ ከሆነ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ
ጥንዶቹ በጋራ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ (Click here to download BOTH FORMS) /ቅፅ-7/
እና /ቅፅ-8/ በሁለት ኮፒ ተያይዞ ሲቀርብ፣
7.አገልግሎቱ የፀና የባል ወይም የሚስት የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እና የትውልድ መታወቂያውን
ለማግኘት በማስረጃነት አቅርበውት የነበረው ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱን
ማስረጃ ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
8.የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ
በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን
መላክ። ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ
መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ። (ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture
FORM)፣ሆኖም ከዚህ በፊት የነበረዎት የትውልድ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪዴብል የነበረ ከሆነና
አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅብዎትም።
9.የአገልግሎት ክፍያ 264.00 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጻፈ መኒ ኦርደር/money order/፣
10.አድራሻዎ የተጻፈበት ቅድሚያ የተከፈለ አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number
ያለው (FEDEX ወይም UPS) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
TOP
ሠ.በጠፋ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ፣
1.መጠየቂያ ቅጽ-4 በሁለት ኮፒ መሙላት (Click here to download)፣
2.መታወቂያው ስለመጥፋቱ በግለሰቡ የተጻፈ ማመልከቻ፣እንዲሁም ከተቻለ ስለመጥፋቱ የሚገልጽ ዝርዝር የፖሊስ
ማስረጃ ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
3.የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት(አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6ወራት የፀና ፓስፖርት) ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ
ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
4.የቀድሞ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ሁለት ኮፒ(የመታወቂያው ኮፒ ከሌለዎ መቼ እና ከየት እንደወሰዱት
የሚገልጽ ማስታወሻ አያይዘው ይላኩ።)
5.ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱን ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ
የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
6.የጠፋው መታወቂያ ካርድ በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ ከሆነ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ የትዳር ጓደኛ
ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ(Click here to download BOTH FORMS)
/ቅፅ-7/ እና /ቅፅ-8/ በሁለት ኮፒ እንዲሁም የባለቤቱ/ቷ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ እና የትውልድ
መታወቂያውን ለማግኘት በማስረጃነት አቅርበውት የነበረው ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች
ውስጥ አንዱን ማስረጃ ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
7.የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ
በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን
መላክ።ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ
መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።(ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture
FORM)፣ ከዚህ ቀደም የነበርዎት የትውልድ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪዴብል የነበረ ከሆነና አሻራ
ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅብዎትም።
8.ሦስት/3/ የፓስፖርት መጠን(3x4cm) ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች
የሚታዩ፣ መደቡ ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም የተጻፈበት)፣
9.የአገልግሎት ክፍያ ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጻፈ መኒ ኦርደር/money order/ ሆኖ
ሀ.በጠፋ ምትክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲሰጥ 316.80 የካናዳ ዶላር፣
ለ.በጠፋ ምትክ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሰጥ 396.00 የካናዳ ዶላር፣
ሐ.በጠፋ ምትክ ለሦስተኛ ጊዜና ከዚያ በላይ ሲሰጥ 528.00 የካናዳ ዶላር፣
10.አድራሻዎ የተጻፈበት ቅድሚያ የተከፈለ አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number
ያለው (FEDEX ወይም UPS) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
TOP
ረ.በተበላሸ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ምትክ ለሚጠይቁ፣
1.መጠየቂያ ቅጽ-4 በሁለት ኮፒ (Click here to download)፣
2.የታደሰ የውጭ አገር ፓስፖርት (አገልግሎቱ ቢያንስ ለ6ወራት የፀና ፓስፖርት) ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ
ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
3.የተበላሸው የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ዋናውን ከሁለት ኮፒ ጋር፣
4.ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱን ዋናውን ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ
የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
5.የተበላሸው መታወቂያ ካርድ በጋብቻ ምክንያት የተሰጠ ከሆነ የኢትዮጵያ ተወላጅ የሆነ የውጭ ሀገር ዜጋ የትዳር
ጓደኛ ትዳሩ የፀና ለመሆኑ ጥንዶቹ የፈረሙት የቃለ-መሃላ ሰነድ (Click here to download BOTH
FORMS) /ቅፅ-7/ እና /ቅፅ-8/ በሁለት ኮፒ እንዲሁም የባለቤቱ/ቷ የኢትዮጵያ ተወላጅነት መታወቂያ ካርድ
እና የትውልድ መታወቂያውን ለማግኘት በማስረጃነት አቅርበውት የነበረው ከላይ በተራ ቁጥር ሀ.3 ሥር
ከተዘረዘሩት ማስረጃዎች ውስጥ አንዱን ማስረጃ ዋናው ሰነድ ወይም በኖታሪ ፐብሊክ የተረጋገጠ ሁለት ኮፒ፣
6.የጣት አሻራ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ወይም የጣት አሻራ ለመውሰድ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች ዘንድ
በመሄድ ድርጅቱ በሚያቀርብላችሁ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ/form/ ላይ አሻራዎን ሰጥተው ዋናውንና ኮፒውን
መላክ።ሆኖም ድርጅቶቹ የጣት አሻራ መውሰጃ ቅጽ ከሌላቸው በኤምባሲው በኩል የተዘጋጀውን የጣት አሻራ
መውሰጃ ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።(ቅፅ-5 Click here to download fingerprint capture
FORM)፣ ሆኖም ከዚህ በፊት የነበረዎት የትውልድ ኢትዮጵያዊነት መታወቂያ ካርድ ማሽን ሪዴብል የነበረ ከሆነና
አሻራ ሰጥተው ከነበረ በድጋሚ አሻራ መስጠት አይጠበቅብዎትም።
7.ሦስት/3/ የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ(ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ
ነጣ ያለና ከጀርባው ሙሉ ስም የተጻፈበት)፣
8.የአገልግሎት ክፍያ 290.40 የካናዳ ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተጻፈ መኒ ኦርደር/money order/፣
9.አድራሻዎ የተጻፈበት ቅድሚያ የተከፈለ አስቸኳይ ወይም የተመዘገበ የካናዳ ፖስታ ወይም Tracking Number
ያለው (FEDEX ወይም UPS) ከነቴምብሩ አብሮ መላክ፣
TOP
በካናዳ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መንግስት በአሁኑ ወቅት በአገራችን በመካሄድ ላይ ካለው ለውጥና ዲያስፖራው በአገሩ ጉዳይ የበለጠ ተሳትፎውን እንዲያሳድግ በሰጠው ትኩረት የዲያስፖራ ጉዳዮችን የሚመራው የስራ ክፍል ከፍ ብሎ ራሱን ችሎ በኤጀንሲ ደረጃ እንዲዋቀር አድርጓል፡፡ ይህ አዲስ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ በይፋ ስራ ለማስጀመር በተለያዩ አገሮች የሚገኙ የዳያስፖራ ተወካዮች በስነ ስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል፡፡
ስለዚህ እ.ኤ.አ ማርች 1 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ በሚካሄደው የ Launching ስነ ስርዓት ላይ ከካናዳ ሁለት የራሳቸውን የትራንስፖርትና ሌሎች ወጪዎችን በመሸፈን ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ የኮሙኒቲ አባላት በኦታዋ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ በስልክ ቁጥር 613-565-6637 Ext. 203 ወይም Ext. 204 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የኢፌዲሪ ኤምባሲ
ኦታዋ ካናዳ
INFORMATION REGRDING THE DIASPORA TRUST FUND
Invitation for Bid
Name of Country: Ethiopia
Name of Project: Procurement of 400,000 MT wheat grain or milling wheat for Ministry of Trade and Industry (Ethiopian Trading Business Corporation).
Procurement Reference number: PPPDS/ETBC/ICB/PG/131/03/2011
(a) Documents will be issued at Ministry of Finance, compound No.2, block 5th, 1stfloor, room No. 101, Telephone 011-1-540524, 011-1-223755/22
(b) Bids must be delivered to, and will be opened at PPPDS, Ministry of Finance, compound No.2, Block No. 5th, 1st floor conference Hall.
PPPDS reserves the right to reject any or all bids and any items on the bid.
Public Procurement and Property Disposal Service (PPPDS)
Tel. 011-1-540524, 011-1-223755 or 011-1-223722
Website; http://www.pppds.gov.et
Addis Ababa, Ethiopia
ለውድ ተገልጋዮቻችን በሙሉ፡-
ኤምባሲያችን በፓስፖርት፣ ቪዛና የሰነድ ማረጋገጫ አገልግሎቶች ላይ ባለው የምንዛሪ ልዩነት የዋጋ ለውጥ ያደረገ መሆኑን እየገለጸ አገልግሎቶቹንና የዋጋ ዝርዝር በተመለከተ በድኅረ ገጻችን Consular Section በሚለው ሜኑ ስር የምታገኙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ
ኦታዋ ካናዳ
ለሁሉም ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን
በካናዳ በጉዲፈቻ መንገድ የመጡ ህፃናትና ወጣቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሚሲዮናችን እነዚህን ዜጎች በማግኘትና ፍላጎት ያላቸውን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት እንዲሁም ያሉበትን ሁኔታ ኤምባሲው ለማወቅና ለመደገፍ ስለፈለገ ይህ መረጃ እንዲደርሳቸውና አድራሻቸውን እንድታሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ስልክ ቁጥር (613) 565 6637 ext 204፣ 207፣ 213
ወይም በኢሜል፡ info@ethioembassycanada.org
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ኦታዋ
Announcement
For all types of Visas /ለሁሉም ዓይነት የቪዛ ጥያቄ /
Use online E-Visa:
https://www.evisa.gov.et/#/home
Announcement [ለውድ ተገልጋዮች!!]
ጉዳዩ፡ የውክልና ሰነዶችን የማረጋገጥ አገልግሎት አሰራር ላይ የተደረገ ለውጥን ይመለከታል፡፡
ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ ያላበቃ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም አገልግሎቱ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዛችሁ ተገልጋዮች ያዘጋጃችሁትን ውክልና ኖታሪ [ Notary] በማድረግ ብቻ ወደ ኤምባሲያችን በመላክ የማረጋገጥ ስራ ስናከናውን መቆየታችን ይታወቃል፡፡ ሆኖም ከሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም [ ከጁን 21/2018] ጀምሮ ማንኛውም ወደ ኤምባሲያችን የሚላኩ ኖታሪ [ Notary] የተደረጉ የውክልና ሰነዶች ወደ ኤምባሲያችን ከመላካቸው በፊት እንደሌሎች ሰነዶች ኦታዋ በሚገኘው የካናዳ ግሎባል አፌየርስ [ Canadian global Affairs in Ottawa ] ከተረጋገጡ በኋላ ወደ ኤምባሲያችን መላክ እንደሚኖርባቸው በአክብሮት መግለጽ እንወዳለን፡፡በሌላ በኩል የውክልና ሰነድ መስጠት ለሚፈልጉ ቫሊድ የሆነ የኢትዮጵያ ፓስፖርትና ትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ ያላቸው ተገልጋዮች ኤምባሲው ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ሰነዱ ላይ በመፈረም በቀላሉ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ቆንስላ አገልግሎት
ለበለጠ መረጃ እባክዎ www.ethioembassycanada.org ይጎብኙ፡፡
EMBASSY OF ETHIOPIA
WASHINGTON DC, USA
ETHIOPIAN CONSULATE GENERAL
LOS-ANGELES, LA, USA
ETHIOPIAN MISSION TO THE UN
NEW YORK, USA
MINISTRY OF FOREIGN AFFAIRS
ADDIS ABABA, ETHIOPIA
Embassy Address:
1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada
Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175
Email: info@ethioembassycanada.org
For consular services
Email: consular@ethioembassycanada.org