No automatic alt text available.

 አገራችን ከአሁን ቀደም ባልታየ መልኩ ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ከፍተኛ የለውጥ እርምጃ ተወስዶ በኢትዮጵያ ሰላም፣ ፍቅር፣ መቻቻልና ይቅርታ በማንገስ ብሔራዊ መግባባትን ፈጥሮ አገራችንን ከፍ ለማድረግ በመሠራት ላይ ይገኛል፡፡ በቅርቡም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ለመላው የአገራችን ህዝቦች እንዲሁም በውጭ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ ይህንን የአንድነት፣ የፍቅር፣ የመቻቻል፣ የሰላምና የይቅርታ ዘመን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያገባኛል በሚል በመደመር አገራችንን ወደ ከፍታ ለማውጣት እንዲቻል የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ክቡር ጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ በአገር ውስጥ በተለያዩ ክልሎችና ከተሞች በመገኘት ለኢትዮጵያውያን ንግግር በማድረግ ህዝቡ በአገራችን ለተጀመረው የአንድነት፣ የፍቅር፣ የሰላም፣ የይቅርታ እንዲሁም ብሔራዊ መግባባት የማስፈን የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ጥሪ ማስተላለፋቸውና የተለያዩ የማህበረሰቡ ክፍሎች ማለትም የሃይማኖት አባቶችን፣ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን፣ አርቲስቶችን፣ የንግድ ማህበረሰቡን፣ ወዘተ በዚሁ አጀንዳ ዙሪያ አወያይተዋል። በቅርቡም ከኢትዮጵያ ውጭ ለሚገኙ የዳያስፖራ አባላት መልዕክት ለማስተላለፍ “ግንቡን እናፈርሳለን፣ ድልድዩን እንገነባለን” በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 21 እና 22 ቀን 2010 ዓ.ም. /ጁላይ 28 እና 29/2018/ በዋሽንግተን ዲሲ እና በሎስአንጀለስ በመገኘት ዳያስፖራውን ፊት ለፊት ለማነጋገር ቀን ተቆርጦ የቅድመ - ዝግጅት ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል። በካናዳ የምትገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላትም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ወደ ሰሜን አሜሪካ መምጣት እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በሰሜን አሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ ሐምሌ 21 ቀን 2010 ዓ.ም. እንዲሁም በሎስአንጀለስ ሐምሌ 22 ቀን 2010 በሚካሄዱ መድረኮች ላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በቦታው ተገኝተው ለዳያስፖራው መልዕክት የሚያስተላልፉ ስለሆነ በስብሰባው ላይ እንድትሳተፉ ጥሪ የተላለፈላችሁ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በተጨማሪም በካናዳ ኦታዋ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ በካናዳ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልድ ኢትዮጵውያን የአመለካከት፣ የብሔር፣ የቋንቋ፣ የእምነትና የጾታ ልዩነት ሳይገድበው በአገራችን በመካሄድ ላይ ለሚገኘው ልማትና ሰላም እንዲሁም አገራችንን ከድህነት ለማውጣት በሚካሄደው ርብርብ በአዲስ ስሜት በአንድ ላይ በመደመር አስተዋፅኦ እንድናበረክትና በአገራዊ ጉዳዮቻችን ላይ ከሁላችሁም ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ይገልፃል። ይህንን ለማስተናገድ ለማንኛውም ኢትዮጵያዊ ኤምባሲው ክፍት መሆኑን ለማረጋገጥ ይወዳል። በአገራችን ጉዳይ ላይ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ለአገሩ የሚበጀውንና የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት ጥሪ እያቀረብን ኤምባሲውና መላው ሠራተኞቹ በቅንነትና በታማኝነት በትብብር ለመሥራት ከፍተኞ ፍላጎትና ዝግጁነት ያለን መሆናችንን እናረጋግጣለን።

ግንቡን እናፈርሳለን፣ ድልድዩን እንገነባለን!

ሁላችንም ተደምረን አገራችንን ከፍ እናደርጋታለን!

በኦታዋ የኢፌዲሪ ኤምባሲ

QUICK LINKS

 

 

ለውድ ተገልጋዮቻችን በሙሉ፡-

 

ኤምባሲያችን በፓስፖርት፣ ቪዛና የሰነድ ማረጋገጫ አገልግሎቶች ላይ ባለው የምንዛሪ ልዩነት የዋጋ ለውጥ ያደረገ መሆኑን እየገለጸ አገልግሎቶቹንና የዋጋ ዝርዝር በተመለከተ በድኅረ ገጻችን Consular Section በሚለው ሜኑ ስር የምታገኙ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ

ኦታዋ ካናዳ

 

 

ለሁሉም ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን

 

በካናዳ በጉዲፈቻ መንገድ የመጡ ህፃናትና ወጣቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ሚሲዮናችን እነዚህን ዜጎች በማግኘትና ፍላጎት ያላቸውን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት እንዲሁም ያሉበትን ሁኔታ ኤምባሲው ለማወቅና ለመደገፍ ስለፈለገ ይህ መረጃ እንዲደርሳቸውና አድራሻቸውን እንድታሳውቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

 

ስልክ ቁጥር (613) 565 6637 ext 204፣ 207፣ 213

 

ወይም በኢሜል፡ info@ethioembassycanada.org

 

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ኦታዋ

 

 

Announcement Agraf

For all types of Visas /ለሁሉም ዓይነት የቪዛ ጥያቄ / 

Use online E-Visa:
https://www.evisa.gov.et/#/home
Announcement [ለውድ ተገልጋዮች!!] Agraf

ጉዳዩ፡ የውክልና ሰነዶችን የማረጋገጥ አገልግሎት አሰራር ላይ የተደረገ ለውጥን ይመለከታል፡፡
ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ ያላበቃ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም አገልግሎቱ ያላበቃ የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዛችሁ ተገልጋዮች ያዘጋጃችሁትን ውክልና ኖታሪ [ Notary] በማድረግ ብቻ ወደ ኤምባሲያችን በመላክ የማረጋገጥ ስራ ስናከናውን መቆየታችን ይታወቃል፡፡ ሆኖም ከሰኔ 14 ቀን 2010 ዓ/ም [ ከጁን 21/2018] ጀምሮ ማንኛውም ወደ ኤምባሲያችን የሚላኩ ኖታሪ [ Notary] የተደረጉ የውክልና ሰነዶች ወደ ኤምባሲያችን ከመላካቸው በፊት እንደሌሎች ሰነዶች ኦታዋ በሚገኘው የካናዳ ግሎባል አፌየርስ [ Canadian global Affairs in Ottawa ] ከተረጋገጡ በኋላ ወደ ኤምባሲያችን መላክ እንደሚኖርባቸው በአክብሮት መግለጽ እንወዳለን፡፡በሌላ በኩል የውክልና ሰነድ መስጠት ለሚፈልጉ ቫሊድ የሆነ የኢትዮጵያ ፓስፖርትና ትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ ያላቸው ተገልጋዮች ኤምባሲው ጽ/ቤት በአካል ቀርበው ሰነዱ ላይ በመፈረም በቀላሉ አገልግሎት ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡   

ቆንስላ አገልግሎት 

ለበለጠ መረጃ እባክዎ www.ethioembassycanada.org ይጎብኙ፡፡


 

USEFUL LINKS

EMBASSY OF ETHIOPIA
WASHINGTON DC, USA

WWW.ETHIOPIANEMBASSY.ORG


ETHIOPIAN CONSULATE GENERAL
LOS-ANGELES, LA, USA

WWW.ETHIOCONSULALA.ORG


ETHIOPIAN MISSION TO THE UN
NEW YORK, USA

WWW.ETHIOPIANMISSION-NY.ORG


MINISTRY OF FOREIGN AFFAIRS
ADDIS ABABA, ETHIOPIA

WWW.MFA.GOV.ET

 


 

Embassy's Address


 Embassy Address:

1501-275 Slater Street, Ottawa Ontario
K1P 5H9 Canada 

Tel (613) 565 6637 / Fax (613) 565 9175

 Email: info@ethioembassycanada.org  

For consular services

Email: consular@ethioembassycanada.org


 

Copy right ©2014 - Embassy of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, Ottawa, Canadan